エピソード

  • የሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    10 分
  • DW Amharic የሚያዝያ 16 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/24
    የኢትዮጵያ ሪፖርተር ጋዜጣ አበበ ፍቅር የተባለ ዘጋቢው የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ለማነጋገር ሲሞክር መታሰሩን አስታወቀ። ኬንያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ደረጃ ለማሳደግ እና የንግድ እንቅፋቶችን ለመቃወም ተስማሙ። በመሐመድ ሐምዳን ደጋሎ በሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተመሠረተ የተባለውን ትይዩ መንግሥት ግብጽ እና ጅቡቲ ተቃወሙ። እስራኤል በጋዛ ሠርጥ በምትገኘው ጃባሊያ በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ሐሙስ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገደሉ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች እንድታቆም ጥሪ አቀረቡ።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/04/23
    የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ትናንት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በጥቃቱ ከባድ መሣሪያዎችም ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ጅቡቲ ሕገ ወጥ ስደተኞችን በቅርቡ ማባረር እንደምትጀምር አስታወቀች። ስደተኞቹ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አዟል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት መሐሙድ አባስ ሀማስ ጋዛ ውስጥ የያዛቸውን ታጋቾች በሙሉ እንዲለቅ ጠየቁ። ታጋቾቹን ይዞ መቆየቱ እስራኤል በፍልስጤም ጥቃቷን እንድትቀጥል ሰበብ ሆኗታል ብለዋል።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    11 分
  • የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    12 分
  • DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/20
    በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓልን አከበሩ። ሩሲያ እና ዩክሬን የተኩስ አቁም በመጣስ እርስ በርስ ተወነጃጀሉ። የእስራኤል ጦር በጋዛ 15 የሕክምና ባለሙያዎች የተገደሉበት ባለፈው ወር የተፈጸመ ጥቃት ላይ በተደረገ ምርመራ በርካታ ሙያዊ ስሕተቶች እና የትዕዛዝ ጥሰቶች መገኘታቸውን ይፋ አደረገ። ከፍራንክፉርት አቅራቢያ ሁለት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የጀርመን ፖሊስ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ዘመቻ እያካሔደ ነው። በሺሕዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፖሊሲዎቻቸውን በመቃወም ኒው ዮርክ እና ዋሽንግተንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አደባባይ ወጡ።
    続きを読む 一部表示
    8 分
  • የሚያዝያ 11 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/19
    የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ አስታወቀ። ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን ቃል ገቡ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ፋሲካን ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠል ተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች።
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • የሚያዚያ 10 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/18
    -በመላዉ ዓለም የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ የሥቅለት በዓልን አክብረዉ ዋሉ።በአሉ ቫቲካን ዉስጥ በርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳቱ ሕመም፣ እየሩሳሌም ዉስጥ በጦርነት መሐል ግን የግሪጎሪያንና የዩሊዮስ የቀን አቀጣጠርን በሚከተለዉ ዓለም ሁሉ አንድ ቀን ተከብሯል።----የእስራኤል ጦር ጋዛ ሠርጥ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ደግሞ የመን ዉስጥ በርካታ ሰዎችን ገደሉ።እስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ ያቀረበችዉን ጥያቄ ሐማስ ዉድቅ አደረገዉ።---የዩክሬንና የሩሲያን ጦርነትን በድርድር ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስ የምታደርገዉ ጥረት ባጭር ጊዜ ዉጤት ካላመጣ ጥረቱን ልታቆም እንደምትችል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    12 分