『የዓለም ዜና』のカバーアート

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

著者: DW
無料で聴く

このコンテンツについて

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2025 DW 政治・政府
エピソード
  • የጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    2025/11/06
    DW Amharic -የዛሬው የዓለም ዜና፤ በአፋር ክልል በትግራይ ሀይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ለጥቂት ቀናት ሲካሄድ የቆየ ነው መባሉን፤የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከ7ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በፊት የሕገመንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ መጠየቃቸው፤አልፋሺር በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከተያዘች ወዲህ ሰባት ጋዜጠኞች የደረሱበት አለመታወቁን፤ሱዳን፤ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በአሸባሪነት እንዲሰየም መጠየቋን፤ደቡብ አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ውስጥ ተሳትፈው ከተያዙ ዜጎቿ የድረሱልኝ ጥሪ እንደደረሳት መግለጿን፤እስራኤል ከግብፅ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የተዘጋ ወታደራዊ ቀጠና ማወጇን ያስቃኛል።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/11/05
    የጀርመን ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት 10 ታማሚዎችን በመግደል ጥፋተኛ በተባለች ነርስ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ፈረደ። ግለሰቧ 27 ሰዎች ላይም የመግደል ሙከራ በማድረግ ጥፋተኛ ተብላለች። ፈረንሳይ ውስጥ በዛሬው ዕለት አንድ ግለሰብ በመኪና ሆን ብሎ በሰዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ተጎዱ። ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የጋዛ ባለሥልጣናት እስራኤል በዛሬው ዕለት የ15 ፍልስጤማውያንን አስከሬን መመለሷን አስታወቁ። ሀማስም ከሁለት ሳምንት በፊት 20 ታጋቾችን እና 21 አስከሬኖችን ለእስራኤል አስረክቧል። የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው የኒኩሊየር የጦር መሣሪያ ሙከራ እንደምትጀምር ዛሬ አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    2025/11/03
    በውዝግብ እና ዓመፅ ያታጀበው የታንዛንያ ምርጫ ማሸነፋቸውን ያወጁት ሳምያ ሱሉሑ ሐሰን በዛሬው ዕለት የፕረዚደንትነት ቃለ መሐላ ፈጸሙ። የጀርመን ፕረዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በጋና የ3 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አክራ ገብተዋል። እስራኤል በሊባኖስ በሁለት ቦታዎች በፈጸመችው የአየር ጥቃት 2 ሰዎች መገደላቸውንና 7 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
    続きを読む 一部表示
    12 分
まだレビューはありません