『DW Amharic የሐምሌ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና』のカバーアート

DW Amharic የሐምሌ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና

DW Amharic የሐምሌ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና

無料で聴く

ポッドキャストの詳細を見る

このコンテンツについて

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ከ50 በላይ ሰዎችን በጅምላ አገቱ። ሩሲያ በዩክሬን ቁጥጥር ሥር በሚገኙት የዶኔትስክ እና ኼርሶን ግዛቶች በሣምንቱ መገባደጃ በፈጸመችው ድብደባ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ዛሬ እሁድ አስታወቁ። የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር በኻን ዩኒስ በሚገኝ ዋና መሥሪያ ቤቱ ላይ በተፈጸመ ጥቃት አንድ ሠራተኛው ሲገደል ሌሎች ሦስት መቁሰላቸውን አስታወቀ። የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ ካያ ኻላስ በሐማስ እጅ የሚገኘው እስራኤላዊ ታጋች ሁኔታ "አስደንጋጭ" ሲሉ አወገዙ። በምሥራቃዊ ሩሲያ ካምቻትካ ግዛት የሚገኝ እሳተ ገሞራ ከ600 ዓመታት ገደማ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈነዳ።
まだレビューはありません