『የዓለም ዜና』のカバーアート

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

著者: DW
無料で聴く

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2026 DW 政治・政府 日次
エピソード
  • የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2026/07/02
    በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሬ ዞን ተማሪዎች እስካሁን የዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና እንዳልተፈተኑ ወላጆች ገለጹ። መምህራኑ «መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለመደጎም ያደረገው ውዝፍ የደመወዝ ጭማሪ በተሟላ ሁኔታ አልተከፈለንም» በሚል ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተብሏል። በሰሜናዊ ናይጀሪያ ማለቂያ ባጣው ግጭት ምክንያት ታይቶ የማይታወቅ ረሀብ መከሰቱን ዛሬ የተመድ አስታወቀ። የኬንያ ፍርድ ቤት በስምንት ተማሪዎች ላይ የግድያ ክስ መሰረተ። ዛሬ ማለዳ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አመለከቱ። 86 ሰዎችም ተጎድተዋል።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2026/07/01
    የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አርእስተ ዜና አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ RSFን በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎችና በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ ። ትውልደ-ኢትዮጵያዊቷ ሶሻል ዴሞክራት ሜላት ኪሮስ ትናንት ማክሰኞ በአሜሪካ በዴንቨር አካባቢ የተካሄደውን ምርጫ አሸነፉ። ሜላት ኪሮስ ለ15 ጊዜ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትን ዲያና ደጌትን ነew ያሸነፉት ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በቀጠር ዋና ከተማ ዶሀ ዛሬ ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል ።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2026/07/23
    የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በሚገኘው አባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊ እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈፀመ በተባለ የድሮን ጥቃት የ2 መነኮሳት ህይወት ማለፉን የገዳሙ አበምኔትና የወረዳዉ ቤተክህነት ኃላፊ ተናገሩ። በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን ዛሬ ቀይ ባህር ላይ በነበሩ ሁለት የሳዑዲ አረብያ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ትናንት የተፈራረሙት ስምምነት ሳዑዲ አረብያ ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት እንዲኖራት የሚጠይቅ መሆኑን ትራምፕ አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    12 分
adbl_web_anon_alc_button_suppression_t1
まだレビューはありません