『የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ』のカバーアート

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

著者: SBS
無料で聴く

このコンテンツについて

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።Copyright 2025, Special Broadcasting Services 社会科学
エピソード
  • ሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማር
    2025/08/30
    ዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችን አንስቶ ይናገራል።
    続きを読む 一部表示
    23 分
  • "ለዛሬ መድረሻዬ ሆነኝ የምለው፤ በስደት ካምፕ የነበረኝና የሰንቅኩት ሕይወት ነው" ዳንኤል አለማር
    2025/08/30
    "የኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ ነው እንዳትነኩት" - ዳንኤል አለማር፤ በግለ ታሪክ ወጉ ገና ለአካለ መጠን ሳይደርስ በለጋ ዕድሜው ከእናትና ወንድሞቹ ጋር እንደምን የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለቅቆ ለኬንያ የስደት ካምፕ እንደተዳረገና የኢትዮጵያ ስም እንደምን ከእሥር እንዳስለቀቀው ነቅሶ ያወጋል።
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • "ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴ
    2025/04/03
    አንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከ Club Kabarett ጋር በመሆን ለሕዝብ ስለምታቀርበው ዝግጅቷ ታነሳለች። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም በሥፍራው እንዲገኙ ትጋብዛለች።
    続きを読む 一部表示
    9 分
まだレビューはありません