『ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት?』のカバーアート

ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት?

ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት?

無料で聴く

ポッドキャストの詳細を見る

【Amazonプライム会員限定】今ならプレミアムプランが4か月 月額99円。

10月19日まで。※適用条件あり
በተደራራቢ ግጭቶች ውስጥ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ ኢትዮጵያ ሌላ የጦርነት ሥጋት ተጋርጦባታል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ስለ ዴሞክራሲ ቢሰበክም የፖለቲካ ልሒቃኑ አገሪቱን ከግጭት አዙሪት ማላቀቅ አልቻሉም። ለምን? የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማቆም የሚችል ወገን አለ? ወይስ ረፍዷል? በአሜሪካው ኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ማወር የሕግ ትምህርት ቤት ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ፈንታው፤ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊ እና በግጭትና መፈናቀል ጉዳዮች ላይ ምርምር የሚያደርጉት ዶክተር ሳሙኤል ዘውዴ በውይይቱ ተሳትፈዋል።
adbl_web_anon_alc_button_suppression_t1
まだレビューはありません