エピソード

  • ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብ
    2026/07/06
    ከዓለም ምጣኔ ሐብት 23 ከመቶዉን ያክል የምትቆጣጠረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ።ዩናይትድ ስቴትስን በሩቅ ርቀት የምትከተለዉ ቻይና፣ ቻይናን እጅግ በጣም ርቃ የምትከተለዉ ጀርመንና ከጀርመን የምትቀጥለዉ የጃፓን ኤኮኖሚ ቢደመር የአሜሪካንን አያክልም።ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ ሊግ ኦቭ ኔሽንስን አፍርሳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በሚጠቅማትና ዓላማዋን በሚያራምድ መልክ አደራጅታለች።
    続きを読む 一部表示
    15 分
  • የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል?
    2026/07/13
    የአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ ድርድር ለመግፋት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አስፈልጓል።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣የሶማሊያ ሠላምና የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የመጨረሻ መጀመሪያ
    2026/07/20
    የአሜሪካ ዉሳኔ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔዎች ጋር መቃረኑ ዋሽግተኖች ለዉሳኔዉ የሰጡትን ምክንያት አጠያያቂ አድርጎታል።አጠያየቀም-አላጠያየቀ የአሜሪካ ዉሳኔ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ብዙዎች እንደሚሉት 20 ዓመት ግድም ላስቆጠረዉ ለአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ተልዕኮ የመጨረሻዉ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል
    続きを読む 一部表示
    14 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ጦርነት-አዳዲሶቹ የጦር ግንባሮች
    2026/07/27
    የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች፣ የቴሕራኖችን ማስጠንቀቂያ ንቀዉ፣ የዲፕሎማት፣ ተንታኖችን ምክር-ማሳሰቢያ አጣጥለዉ የካቲት 28፣ 2026 ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስድስተኛ ወሩ ሁለተኛ የዉጊያ ግንባር አስከፈተ። የባብ ኤል መንደብ ወሽመጥን አዘጋም።ሥልታዊዉ ወሽመጥ የአፍሪቃ፣ የእስያና የአዉሮጳ የባሕር መስመር ሕልቅት ነዉ። በባሕር ከሚተላለፉ የዓለም ሸቀጦች ከ12 ከመቶ በላይ ይመላለስበታል።ከዓለም የኢንተርኔት መስመር 17 ከመቶዉ ተዘርግቶበታል።
    続きを読む 一部表示
    14 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል
    2026/08/03
    ከሰኔ 30 በኋላ ከህወሐት ያፈነገጠዉ አንጃ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጆችና ደጋፊዎቻቸዉን «ጦርነት አንፈልግም» በሚል በአደባባይ ሲያሰልፍ፣ መቀሌ ዉስጥ ደግሞ ህወሓት የጠራዉ ተቃራኒ ህዝባዊ ሥብሰባ ተደርጓል።ስልፍና ስብሰባዉ የቃላት ጦርነቱን ወደየደጋፊዎቻቸዉ ለማስረፅ ያለመ መሆኑ አላከራከረም። የህወሐት ዋና ፀሐፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ወጣቶች «አሁን ብቻችን አይደለንም» ማለታቸዉ ግን ከቃል አቀባያቸዉ አባባል ጋር የሚጣረስ በተገላቢጦሹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን ወቀሳ የሚያረጋግጥ ነዉ
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙ
    2026/08/10
    አፍሪቃ «የራስዋን ችግር በራስዋ መፍታት የመቻሏ» አብነት፣ ኢትዮጵያዉያን እንደሚዋጉት ሁሉ «ለሰላማዊ ዉል ለመገዛትም ፈቃደኛ የመሆናቸዉ» ምሳሌ ተደርጎ ብዙ የተነገረለት የፕሪቶሪያ ሥምምነት ተኩስ ከማስቆሙ እኩል የአዲስ የኃይል አሰላለፍ ምክንያት መሆኑ ነዉ ዚቁ።የተፋላሚ ኃይላት ዋና ተዋኞች በሥምምነቱ ይዘት፣አተረጓጎምና ገቢራዊቱ ላይ ከመነጋገር፣ ለመግባባት ከመጣር ይልቅ አጋር ፍለጋ ሲቃትቱ ከሶስት ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል።
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ እብሪት፣ በፍርሐት የተጠፈነገዉ ዓለምና የአፍሪቃ ፈተና
    2026/08/17
    የሆርሙዝ ወሽመጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ በተለይ አፍሪቃ በማታዉቀዉ፣በማያገባትና በማትፈልገዉ ጦርነት የርዳታ ተመፅዋች ዜጎችዋን ሕይወት እንድትከፍል አስገድዷታል።ከኢትዮጵያ እስከ ናጄሪያ፣ ከሶማሊያ እስከ ሴኔጋል የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የርዳታ እሕል፣ መድሐኒት፣ቁሳቁስ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦባቸዋል
    続きを読む 一部表示
    15 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የ4 ዓመታት ዝግጅት፣የ40 ቀናት ጉባኤ-ለኢትዮጵያ ይበጅ ይሆን?
    2026/08/24
    ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተጠናቀቀዉ ምክክርም ህወሓትን ይዞ፣ ፋኖን፣ ኦነሠን፣ የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ክልሎች አማፂያንን አክሎ፣ ገሚስ-ኦብነግን፣ እንደ ኦነግ፣ ኦፌኮ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ከሐገር ዉጪ የሚገኙ የፖለቲካ፣ የአካባቢ፣ የመብት ተሟጋቻች ማሕበራትን ጨምሮ አራት አመታት በፈጀዉ የምክክር ሒደት አልተካፈሉም
    続きを読む 一部表示
    22 分