『DW Amharic የታኅሳስ 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና』のカバーアート

DW Amharic የታኅሳስ 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና

DW Amharic የታኅሳስ 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና

無料で聴く

ポッドキャストの詳細を見る

このコンテンツについて

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ዒድሪስ ጦርነት በሚካሔድባቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ወደ ኒው ዮርክ አቀኑ። የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ቦላ ቲኑቡ የሀገራቸውን የጸጥታ ተቋማት በከፍተኛ ሁኔታ ለማጠናከር ቃል ገቡ። አንድ ኤርትራዊን ጨምሮ አራት ሰዎች ባለፈው አንድ ሣምንት በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት እና የጉምሩክ መስሪያ ቤት በእስር ላይ ሳሉ መሞታቸውን የሀገሪቱ መንግሥት መረጃ ይፋ አደረገ። የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ ከጎርጎሮሳዊው 2028 በኋላ በየአራት ዓመቱ እንደሚካሔድ ተወሰነ።
まだレビューはありません